የኅብረቱ አጀማመርና ታሪካዊ አመጣጥ
በ7ኛ ቀን አድቬንቲስት ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን የወላይታ ዞን የሦስቱ መላዕክት መልዕክት አብሳሪዎች ኅብረት/3 Angels’ Message Messengers Union/ በደቡብ ኢትዮጵያ ሰበካ፣የቀድሞ ወላይታ አውራጃ ንዑስ ሰበካ፣አሁን ደግሞ በ2008 አዲሱ የዲስትሪክቶች አወቃቀር መሰረት ከሦስቱ የወላይታ ንዑስ ሰበካዎች/ምዕራብ ወላይታ ንዑስ ሰበካ፣መካከለኛው ወላይታ ንዑስ ሰበካና ምስራቅ ወላይታ ንዑስ ሰበካ/የተውጣጡ የመንግስትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ኅብረት ሰብስብ ለወንገል ሥርጭት አገልግሎት ቤተ–ክርስቲያኒቱ/የቀድሞ ወላይታ ንዑስ ሰበካ ከ2006 ዓ/ም ጀምሮ ያዋቀረችው ኅብረት ነው፡፡ኅብረቱ ከ2005-2006 ዓ.ም ክረምት በወላይታ ዉስጥ በተለያዩ አካባቢዎች/በጉኑኖ፣በሰላምበር፣ በሶዶ ከተማ እና በሶዶ ዙሪያ በቡጌ ዋንቼ/ የክረምት የወንጌል ዘመቻ ላይ በንዑስ ሰበካው መሪነት የተሳተፈ ሲሆን በእግዚሀብሔር እርዳታ ለብዙ ነፍሳት የዕውነትን ወንጌል መስክሯል፤በቁጥር ጥቂት የማይባሉ ነፍሳትም ከስህተት ጎዳና አምልጠው ወደ ጌታ መንግስት ተጨምሯል፡፡
ኅብረቱ በ2007 ክረምት በድስትሪክቱ መሪነት ስለቤተክርስቲያኒቱ ተልዕኮና ስላለባቸው ሃላፊነት በጉኑኖ ከተማ 7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን በጥልቀት ከተወያየ በኋላ ለሥራዉ ካላቸው መነቃቃትና ግለት እንዲሁም ከክርስቶስ ዳግም ምጽአትና ከዘመኑ ማለቅ አንጻር እንደ ኅብረት በመደራጀት ወንገልን በምድር ለሚኖሩ ሁሉ በታላቅ ፍጥነትና በኃይል መመስከር አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት በወቅቱ በቁጥር 40 ከሚሆኑ አባላት መካከል የቤተ–ክርስቲያኒቱ መምሪያ በሚፈቅደው መሰረት 5 አባላትን የያዜ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተመርጧል፡፡መነሻ የአባላቱ መዋጮም በአመት 50 ብር እንዲሆን በሶዶ ቤተ–ክርስቲያን በሙላጉባኤ ተወስኖ የማሰባሰብ ሥራ ተጀምሯል፡፡ይሁን እንጂ ሁሉም ተማሪ በየዩኒቨርስቲ ተበታትኖ በመቆየቱ፣እስከ 2008 ክረምት ድረስ የባንክ አካውንት ባለመከፈቱና በየዩኒቨርሲቲዎች ተወካይ ባለመኖሩ ሥራው በታሰበለት መጠን ሳይሳካ ቀርቷል፡፡
በሐምሌ 2008 ክረምት እንደገና በጉኑኖ ከተማ በ34 የኅብረቱ አባላት ለአንድ ሳምንት በተደረገው የወንጌል ዘመቻ ኅብረቱ ዛሬ የሚጠራበትን “በ7ኛ ቀን አድቬንቲስት ዓለም አቀፍ ቤተ–ክርስቲያን የወላይታ ዞን የሦስቱ መላዕክት መልዕክት አብሳሪዎች ኅብረት/3 Angels’ Message Messengers Union/”የሚለው ስያሜ እቦታዉ ከቀረቡት ብዙ አማራጮች አብላጫውን ድምጽ አግኝቶ ፀድቋል፡
ምንም እንኳ ኅብረቱ በጥቅት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወንጌልን በዘመቻ በመመስከር የጀመረ ብሆንም እያደር የሥራዉ ጥልቀትና ስፋት፣ የአባላት ቁጥር፣ የወንጌል ስርጭት አድማስ፣ ወዘተ እየጨመረ በመሄዱና ኅብረቱም የአንድ ወቅት ቡድኖች ስብስብ ሳይሆን ዘላቂ እንዲሆን በህጋዊ መንገድ ማደራጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የኅብረቱን ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ ዓላማና ዋና ዋና ተግባራት፣ መዋቅራዊ አደረጃጀት፣ የሥራ ዘርፎች/ዲፓርትሜንቶች ክፍፍል፣ የሥራ መዘርዝር/Job Description/፣ የአባሉ መብትና ግዴታን ወዘተ ያካተተ መተዳደሪያ ደንብ ማዘጋጀት ተችሏል ፡፡ ይህ መተዳደሪያ ደንብ በኅብረቱ ጠቅላላ ጉባኤ 2ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ምልዓተ–ጉባኤ ማለትም የሰበካው ተወካይ፣ የ4ቱ ዞኖች መሪዎች፣ የ4ቱም ዞን ወንጌላዊያንና የ3መመአኅ መላው አባላት በተገኙበት የጋራ መመሪያችን ይሆን ዘንድ በመስከረም 06/2010 ዓ/ም በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡ በመቀጠልም ህብረቱ በቀን 14/9/2010 ዓም በደቡብ መካከለኛ ኢትዮጵያ ሰበካ ህጋዊ እዉቅና በማግኘት እንዲሁም የቤተክርስትያኒቱን አሰራር፣ ደንብ እና መመሪያ በጠበቀ መልኩ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።