ዓላማዎች
ዓላማ፡- ማንኛውም የክርስቶስ ፍቅር ግድ የሚለው ሰው የዘለዓለም ወንጌል የሆነውን የሦስቱን መላዕክት መልዕክት ለዓለም ማዳረስና ለክርስቶስ ዳግም ምጽዓት ነፍሳትን ማዘጋጀት እንዲችልና በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት መጀመሪያ ራሱ እንዲነቃ ቀጥሎ ሌላውን እንዲያነቃ እና ደቀ-መዝሙር እንዲያደርግ ማስቻል ነው፡፡ “አንተ የሚትተኛ ንቃ……..” አፌ 5፡14፤ ማቴ 28፡19-20
ዝርዝር ዓላማዎች፡- ‘’ራስህን አድን፤ወደ ኋላም አትይ’’ ዘፍ 19፡17
- ራስን መስጠት/ማዳን- እያንዳንዱ አባል በግል ህይወቱ ማደግ፣መቀደስ፤ከዓለም ርኩሰት መለየት (ኢያ 3፡5 እና ኢሳ 52፡1)
- ቤተሰብን ማዳን- እንደ ኖህ ቤተሰባችንን ይዘን ወደ መርከብ መግባት፤
- ቤተ-ክርስቲያንን ማዳን- ያለንባትንና ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና ከዛም ወደየሥራ መስኮቻችን በምንሄድበት ጊዜ የምናገኛትን ቤተ-ክርስቲያን ማጽናት፣
- ሌሎችን ማዳን-አባሎቻችን በትምህርትና በሥራ ምክንያት በሚሄዱበት አዳዲስ አካባቢዎች ላይ ወንጌልን መመስከርና ነፍሳትን በማጥመድ ቤተ-ክርስቲያንን መገንባት፤